በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ ተጎበኙ

157

ሰኔ 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ በዛሬው ዕለት ተጎበኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት የተጀመሩት በ1 ወር ከ20 ቀናት ዉስጥ ሰው ተኮር የተቀናጀ የልማት ስራዎች የሚከናወኑባቸውን ሞዴል ክፍለከተሞች የመፍጠር ተግባር እየተከናወነ እንደሆነ ተገልጿል።

May be an image of 4 people, people standing and outdoors

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት፤ በቂርቆስና ልደታ ክፍለከተሞች ብቻ ሁለት ባለ 11 እና 5 ወለሎች 345 ቤቶች የያዙ ፎቆች፣ 20 የዳቦ እና የአታክልት መሸጫ ሱቆች፣ 200 ቦታዎች ላይ የተሰሩ ሞዴል የከተማ ግብርና፣ 8 የዳቦ ፋብሪካዎች፣ 9 የእሁድ ገበያዎች፣ 2 የስፖርት ሜዳዎች ማልማት፣ 4 ፓርኮች ማልማት፣ 5 የመመገቢያ ማዕከላት፣ 15 አደባባዮች ማልማት እንዲሁም 8 ዋና መንገዶች ማስዋብ ስራዎች ይገኛሉ።

May be an image of 8 people, people sitting and people standing

ሁሉም ስራዎች በሃምሌ ወር ተጠናቀው ለተጠቃሚዎች አገልግሎት እንደሚሰጡም ጠቁመዋል።

በይቻላል መንፈስ እየተከናወኑ ያሉ ሞዴል ሥራዎች በሁሉም ክፍለከተሞች ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስነብበዋል።