ፓሪስ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ አሸነፈ

247

ሰኔ 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) ምሽቱን በፓሪስ በተካሄደው ሰባተኛ ዙር የዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ አሸንፏል።

በወንዶች ምድብ በተካሄደው 5 ሺህ ሜትር የፓሪስ ዳይመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ ርቀቱን በበላይነት ሲያጠናቅቅ አትሌት ሙክታር እድሪስ ደግሞ 3ኛ ሆኗል፡፡

በ3000 ሜትር መሰናክል የሴቶች ውድድር የተካፈሉት አትሌት ሲምቦ አለማየሁ እና አትሌት መቅደስ አበበ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ሲያጠናቅቁ ለባህሬን የምትሮጠው ትውልደ ኬንያዊቷ ዊንፍሬድ ያቪ አንደኛ ወጥታለች።

May be an image of 3 people