ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ሀዋሳ ገቡ

1

ሀዋሳ፣ ሰኔ 10 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ሀዋሳ ገብተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀዋሳ ሲደርሱ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የባህል አባቶችና ወጣቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው እለት በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ የልማት ስራዎችን መጎብኘታቸው ይታወቃል።

በጉብኝታቸውም በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ከ55 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ ያለውን የዳቦና ዱቄት ማምረቻ ፋብሪካ ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ