የጤና ሚኒስቴር ዲጂታላይዝድ የጤና መረጃ አያያዝ መተግበሪያ ይፋ አደረገ

152

ሰኔ 10/2014/ኢዜአ/ የጤና ሚኒስቴር ዲጂታላይዝድ የጤና መረጃ አያያዝ መተግበሪያ ይፋ አደረገ፡፡

ሚኒስቴሩ መተግበሪያውን  ወደ ስራ ለማስገባት "ማስተር ካርድ፣ጋቪ እና ከ ጄ ኤስ አይ" ከተሰኙ ተቋማት ጋር ዛሬ ስምምነት ተፈራርሟል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በዚሁ ወቅት መተግበሪያው በጤናው ዘርፍ ያለውን የመረጃ ስርዓት ለማዘመን እንደሚረዳ ገልፀዋል።

"ማስተርካርድ ዌልነስ ፓስ" የተሰኘው ይህ መተግበሪያ  ለ15 ወራት የሚቆይ የሙከራ ምዕራፍ በመላ አገሪቱ በተመረጡ የጤና ተቋማት ላይ የሚተገበር ይሆናል ነው ያሉት።

የመጀመሪያ የሙከራ ትግበራ ምዕራፍ በኮቪድ-19 ክትባት ክትትል መረጃ አያያዝ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ጠቅሰው፤ ሁለተኛው የትግበራ ምዕራፍ ደግሞ በተለያዩ የጤና አጠባበቅ መርሃ-ግብሮች ላይ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በመጀመሪያው የሙከራ ትግበራ ምእራፍም 1 ሚሊዮን ታካሚዎችን ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም