የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላት ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ካቢኔ አባላት ጋር እየተወያዩ ነው

127

ሐዋሳ፤ ሰኔ 10/2014 (ኢዜአ)፡ የብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያን ጨምሮ የኮሚሽኑ አባላት ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ከክልሉ ካቢኔ አባላት ጋር በሐዋሳ እየተወያዩ ነው።

የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ   ባለፉት ሶስት ወራት በኮሚሽኑ የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ገለጻ እያደረጉ ነው።

በመድረኩ በቀጣይ በኮሚሽኑ በሚከናወነው ስራ ክልሎች በሚኖራቸው ድርሻ ላይ ውይይት ይደረጋል።

በመድረኩ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞና የክልሉ የካቢኔ አባላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የኮሚሽኑ አባላት ከከልሉ ወጣቶችና ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም