ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተገኙ ስኬቶችን በማጎልበት ምርቶቻችን በኮንትሮባንድ ድንበር ተሻግረው እንዳይወጡ መከላከላችንን መቀጠል አለብን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

110

ሰኔ 08 ቀን 2014 (ኢዜአ) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተገኙ ስኬቶችን በማጎልበት ከብቶቻችን፣ ቡናችን፣ ወርቃችን እና የሰብል ምርቶቻችን በኮንትሮባንድ ድንበር ተሻግረው እንዳይወጡ መከላከላችንን መቀጠል አለብን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመለከቱ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት "ድንበር ተሻጋሪ የኮንትሮባንድ ንግድ ሀገራችን ከህጋዊ ንግድ የምታገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚያሳጣ ትልቅ ፈተና ሆኖ ቆይቷል" ብለዋል።

በዚህም "ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተገኙ ስኬቶችን በማጎልበት ከብቶቻችን፣ ቡናችን፣ ወርቃችንን እና የሰብል ምርቶቻችን በኮንትሮባንድ ድንበር ተሻግረው እንዳይወጡ መከላከላችንን መቀጠል" አለብን ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም