ተቋማቱ ከ 30ሺህ በላይ መጻህፍትን ለአብረሆት ቤተ-መጻህፍት አስረከቡ

200

ሰኔ 08 ቀን 2014 (ኢዜአ) የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚንስቴር ፣ ሪቫ ካፕ ፋውንዴሽንና የአዲስ አበባ ምክር ቤት ለአብረሆት ቤተ-መጻህፍት 30 ሺህ 703 መጻህፍትን ለአብረሆት ቤተ-መጻህፍት አስረከቡ፡፡

የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚንስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋኢዛ መሀመድ እንዲሁም የሪቫ ፋውንዴሽንን በመወከል ቃል አቀባይ አቶ አክሊሉ ታደሰ መጻህፍቱን አስረክበዋል።

ሪቫ ካምፕ ፋውንዴሽን 28ሺህ 638 መፃህፍትን ያሰባሰበ ሲሆን የአዲስ አበባ ምክር ቤት 1ሺህ 200 መጻህፍት እንዲሁም የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚንስቴር 865 መጻህፍትን ነው ያሰባሰቡት።መጻህፍቱን የተረከቡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መጻህፍቱን ላበረከቱት ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም