በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው ልዑክ አቀባበል ተደረገለት

58

ሰኔ 8 ቀን 2014 (ኢዜአ) በሞሪሺየስ በተካሄደው 22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው ልዑክ አቀባበል ተደርጎለታል።

ኢትዮጵያ 22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በ4 ወርቅ፣ 6 ብር እና 4 ነሐስ በድምሩ 14 ሜዳሊያ በመሰብሰብ 5ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

በዚህ ሻምፒዮና የተካፈለው ልዑክ አዲስ አበባ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትን ጨምሮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስራ አስፈፃሚ አባላት በተገኙበት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ቡድኑ በአዲስ አበባ አራራት ሆቴል የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት የሚሰጠው ይሆናል።