የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመንገደኞች አገልግሎት የአፔክስ 2022 ሽልማትን አሸነፈ

2

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመንገደኞች በሚሰጠው የመዝናኛና የጉዞ ውስጥ መስተንግዶ ተመራጭ በመሆን የአፔክስ 2022 ሽልማት አሸነፈ፡፡

አየር መንገዱ ከሌሎች መሠል አየር መንገዶች ጋር ተወዳድሮ ሽልማቱን ያሸነፈው ለመንገደኞች በሚያቀርበው የጉዞ ክብካቤና ምቾትን ማዕከል ባደረገ አገልግሎቱ ነው ተብሏል፡፡

በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተለያዩ አየር መንገዶች ለተሳፋሪዎቻቸው በሚያቀርቡት መስተንግዶ እንደየደረጃቸው ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

የዚህ ዓመት ሽልማት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠው 600 በሚደርሱ ባለ 5 ኮከብ ማዕረግ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች ውስጥ ከተሳፈሩ መንገደኞች በተሰበሰበ 1 ሚሊየን የዕርካታ ደረጃ አመላካች ድምፅ ነው፡፡

የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ በአየርላንድ ዋና ከተማ ደብሊን መካሄዱን ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።