ኢትዮጵያና ጣሊያን የ22 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት ተፈራረሙ

4

ሰኔ6/2014/ኢዜአ/ ኢትዮጵያና ጣሊያን የ22 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴና የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዋጂ ዲ ማዩ ተፈራርመዋል።

ገንዘቡም ቡልቡላ፣ ቡሬ፣ይርጋለምና ባዕከር ለሚገኙ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ማጠናከሪያ እንዲሁም በፓርኮቹ ዙሪያ ለሚቋቋሙ የገጠር ሽግግር ማዕከላት ግንባታ የሚውል ነው።

May be an image of 7 people and people standing

የብድር ስምምነቱን የጣሊያን እና ኢትዮጵያ ያላቸውን ኢኮኖሚ ትብብር የሚያጠናክር መሆኑንም ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ገልፀዋል።

የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዋጂ ዲማዩ በበኩላቸው ስምምነቱ ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን አጋርነት እንደሚያሳይ  አብራርተዋል፡፡

የብድር ስምምነቱ  በኢትዮጵያ እየተተገበረ ለሚገኘው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስኬታማነት እንደሚያግዝም ገልፀዋል።