የግብርና ዘርፍን ለማዘመን ያለመ የፈጠራ ስራ ውድድር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

2

ሰኔ 6 ቀን 2014 (ኢዜአ) የግብርና ዘርፍን ለማዘመን ያለመ የፈጠራ ስራ ውድድር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

ውድድሩ “አዩቴ ኢትዮጵያ ቻሌንጅ” የሚሰኝ ሲሆን፤  ሃይፈር ኢንተርናሽናል የተሰኘ ድርጅት ነው ያዘጋጀው፡፡

የውድድሩ ዋነኛ ዓላማ አነስተኛ ማሣ ያላቸውን አርሶአደሮች ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያግዙ የፈጠራ ሐሳቦችን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችል ድጋፍ ማድረግ መሆኑ ተገልጿል።

በዛሬው እለትም በውድድሩ ለመካፈል ከተመዘገቡት 535 ተወዳዳሪዎች  መካከል ለመጨረሻ ዙር ያለፉት አምስት ዕጩዎች የፈጠራ ስራዎቻቸውን ይዘው ቀርበዋል፡፡

በውድድሩ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች  10 ሺህ፣ 6 ሺህ 500 እና 3 ሺህ 500  ዶላር   እንደቅደም ተከተላቸው የሚሸለሙ ይሆናል፡፡