ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

8

ሰኔ 6 ቀን 2014 (ኢዜአ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የአገራቱን ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በተለይም በሀገራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

የጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ጣልያን ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር አላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።