3ኛው የኢትዮ-ናይጄሪያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ ተጀመረ

4

ሰኔ 6 ቀን 2014 (ኢዜአ) 3ኛው የኢትዮ- ናይጄሪያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በናይጄሪያ ባደረጉት ጉብኝት የሁለቱን አገራት ግንኙነት የሚያጠናክሩ ስምምነቶችን አድርገዋል፡፡

ከስምምነቱ አንዱ የሁለቱ አገራት የጋራ ኮሚሽን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በአዲስ አበባ ስብሰባው እንዲካሄድ መወሰኑ አንዱ ነው፡፡

በዛሬው ዕለትም ሁለቱ አገራት በንግድ፤ሳይንስና ቴክኖሎጂ፤ማዕድንን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እየመከሩ ነው፡፡

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2006 በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

ሁለተኛው ስብሰባ ደግሞ በ2017 በናይጄሪያ አቡጃ መካሄዱን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡