አማራ ባንክ የአክሲዮን ማህበር ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ሥራውን በይፋ ይጀምራል

724

ሰኔ 6 ቀን 2014 (ኢዜአ) አማራ ባንክ የአክሲዮን ማህበር ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር አስታወቀ።

አማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር በ6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ስራውን በይፋ እንደሚጀምር አስታወቀ።

የባንኩን ስራ የመጀመር ሂደትን አስመልክቶ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች መግለጫ ሰጥተዋል።

በ6 ቢሊዮን 516 ሚሊዮን ብር በላይ በተከፈለ የመነሻ ካፒታል እንዲሁም ከ4 ቢሊዮን 825 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ገንዘብ ተጨማሪ አቅም በማሳደግ ባንኩ ለስራ ዝግጁ መሆኑን የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፈንታ ገልጸዋል።

ባንኩ በ70 ቅርንጫፎች ስራውን የሚጀምር ሲሆን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የቅርንጫፍ ቁጥሩን ወደ 100 ለማሳደግ አቅዷል።

ባንኩ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ባለአክሲዮን መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

ከመደበኛው የፋይናስ አገልግሎት በተጨማሪ "ከባንክ ባሻገር" በሚል የማህበረሰቡን ሕይወት ለማሻሻል የተለያዩ አማራጮችን ማዘጋጀቱንም አክለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም