የአፋርና የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ የሰላም ውይይት ማጠቃለያ መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው

3

ሰኔ 5 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአፋርና የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ የሰላም ውይይት ማጠቃለያ መድረክ በአዳማ አባ ገዳ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ነው።

መድረኩ በሁለቱ ማህበረሰብ መካከል ያሉ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ማምጣት አላማ ያደረገ ነው ተብሏል።

በውይይቱ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፣የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ የፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።