በነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋለው የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር እንዲፈታላቸው የሀረር ከተማ የታክሲ አሽከርካሪዎች ጠየቁ

180

ሀረር ሰኔ 5/2014 (ኢዜአ) በህገወጥ ተግባርና ላይ የተሰማሩና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መጉላላት በሚፈጽሙባቸው የነዳጅ ማደያዎች ላይ መንግስት ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ እንዲያስተካከልላቸው የሀረር ከተማ ታክሲ አሽከርካሪዎችና ባለ ንብረቶች ጠየቁ።

በሀረሪ ክልል በከተማ ታክሲ አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ዙሪያ ከአሽከርካሪዎችና የተሽክካሪ ባለ ንብረቶች ጋር የክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ጨምሮ ባለድርሻዎች አካላትን ያካተተ ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ የተሳተፈው የታክሲ አሽከርካሪ ወጣት አብዱሰላም ሃሰን እንዳለው በከተማው የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከቀኑ ስድስት ሰዓት ቡኋላ አገልግሎት እንደሚይሰጧቸውም ተናግሯል።

ማደያዎቹ ጭለማን ተገን በማድረግ ነዳጁ በበርሜልና ጄሪካን በመቅዳት እየሸጡ እንደሚገኝም ነው የጠቆመው።

በዚህም ከህገወጦች ላይ በሃይላንድ ላስቲክ በመግዛት ለመጠቀም መገደዳቸውን ጠቅሶ መንግስት የሚያደርገውን ቁጥጥር እንዲያጠናክርና ህግን እንዲያስከብር  ጠይቋል።

ወጣት አብዱሰላም በበኩሉ በሰጠው አስተያየት "ማደያዎቹ የመኪና ዘይት ካልገዛችሁ ነዳጅ አንሸጥም እያሉ ያጉላሉናል " በማለት ነው ቅሬታውን ያቀረበው፡፡

በከተማ በታክሲ ስራ ላይ የተሰማሩ ሹፌሮች የትራንስፖርት ተቆጣጣሪዎች ህግን ተገን በማድረግ ታክሲዎችን በማስቆም ገንዘብ የሚጠይቁ መኖራቸውን የገለጹት ደግሞ ኢብራሂም አብዲ የተባሉ የታክሲ አሽከርካሪ ናቸው።

የውይይቱ ተሳታፊ አሽከርካሪዎቹና በለንብረቶች የሚመለከተው የመንግስት አካል ለችግር መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋለ።

የክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ ኢንጅነር ጠይባ አብደላ በመድረኩ የተነሱት ችግሮች ትክክለኛ መሆቸውን አረጋግጠው፤ ቢሮው በሚደሱት መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ክትትል በማድረግ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ  መጀመሩን አስታውቀዋል ፡፡

ቢሮው ችግሩን በሚፈጥሩ ተቆጣጣሪዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥሉ ጠቅሰው የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ አስከርካሪዎች በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉባቸውን ችግሮች ሊቀርፉ እንደሚገባ አሳስበዋል ፡፡

የክልሉ ንግድ ልማት ኤጀንሲ ሃላፊ አቶ ቡሽራ አሊይ ከነዳጅ ማደያዎች ጋር ተያያዘ ለተነሱት ቅሬታዎች በሰጡት ምላሽ ህገወጥ ተግባሮች በሚፈጽሙ ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በዘርፉ የሚስተዋሉ ህገወጥ ተግባራትን በመዋጋቱ ተግባር ላይ የታክሲ አሽከርካሪዎችና መላው ህብረተሰብ ለሚመከለተው የመንግስት ጥቆማ በመስጠት ትብብር ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።  

የነዳጅ ድጎማ የሚደረግላቸው የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ የከተማ ታክሲ ባለንብረቶች አስፈላጊውን ማስረጃ በሟሟላት እንዲመዘገቡም ጥሪ ቀርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም