ኮርፖሬሽኑ በቀበና ሳይት ያስገነባውን የመኖሪያ ቤት ፕሮጀክት አስመረቀ

2

ሰኔ 05 ቀን 2014 (ኢዜአ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በመዲናዋ በቀበና ሳይት ያስገነባውን የመኖሪያ ቤት ፕሮጀክት አስመረቀ፡፡

ፕሮጀክቱ ሚኒስትሮች፣ ሚኒስትር ዴታዎች እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማልና  ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የተመረቀው፡፡

ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት የውል ጊዜ፣ ወጪና ጥራት የተገነባ ሲሆን፤  ሁለት ባለ አስር ወለል ህንጻዎችን የያዘ ነው፡፡

ህንጻዎቹ  70 ካሬ ሜትር እስከ 185 ካሬ ሜትር የሚደርሱ ከባለ 1 እስከ ባለ 4 መኝታ ክፍል ያላቸው  ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ያካተቱ መሆናቸውም ነው የተጠቆመው፡፡

ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 1 ሺህ 727 ካሬ ሜትር ይዞታ ያለው ሲሆን፤  ከዚህም ውስጥ ህንጻዎቹ በ1 ሺህ  167 ካሬ ሜትር ላይ ያረፉ ናቸው።

በተመሳሳይ ኮርፖሬሽኑ በዛሬው እለት ለኢትዮጵያ የግንባታ ፕሮጀክት አዲስ ተክኖሎጂ ያስተዋወቀውን የገርጂ መኖሪያ መንደር ግንባታ ፕሮጀክትን የሚያስመር ይሆናል፡፡