በፍራፍሬ ግብርናው የተገኘው ምርት ተስፋን የሚሰጥ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

44

ሰኔ 4 ቀን 2014 (ኢዜአ) “በፍራፍሬ ግብርናው የተገኘው ምርት ተስፋን የሚሰጥ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የፍራፍሬ ልማቱ አበረታች የሆነ ውጤት እያሳየ ነው ብለዋል።

አዳዲስ የፍራፍሬ ዝርያዎች እየለሙ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

የመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ትናንት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ በመስኖ ልማት 150 ሚሊዮን ኩንታል የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት መሰብሰቡን መግለጻቸው የሚታወስ ነው።

በመደበኛ መስኖ ልማት አትክልትና ፍራፍሬ ልማት 655 ሺህ ሄክታር መሬትን ለማረስ ታቅዶ አንድ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለዚሁ ስራ ማዘጋጀት መቻሉንም አመልክተዋል።