በዱከም ከተማ የተገነባው ታዳሽ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ተመረቀ

3

ሰኔ 04 ቀን 2014 (ኢዜአ) በኦሮሚያ ክልል ዱከም ከተማ የተገነባው ታዳሽ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ዛሬ ተመርቋል።

በምርቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕስ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጅነር ታከለ ኡማ፣ የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

No photo description available.

ፋብረካው በ5 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ካፒታል የተገነባ ሲሆን በ50 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ነው፡፡

ፋብሪካው ለ700 ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።

ፋብሪካው በቀን 600 ቶን ፌሮ ብረት የሚያመርት ሲሆን በተጨማሪም በቀን 450 ቶን ብረት የማቅለጥ አቅም አለው፡፡