የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ያስገነባው የረገ ኤያት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

4

ሰኔ 04 ቀን 2014 (ኢዜአ) የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ያስገነባው የረገ ኤያት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።

በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

May be an image of 8 people, people standing and outdoors

ትምህርት ቤቱ በውስጡ 10 መማሪያ ክፍሎች ፣ ቤተ -ሙከራ፣ ቤተ-መጻሕፍት፣ የተማሪ ክሊኒክ ፣የአስተዳደር ሕንጻና የስብሰባ አዳራሽ ያካተተ ነው ።

የቀዳማዊ እመቤት ጽህፈት ቤት ከዚህ ቀደም በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ማመዴ ቀበሌ ትምህርት ቤት አስገንብቶ ማስመረቁ የሚታወስ ነው።