“በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የከተማዋን የቤት ችግር ለመፍታት የሚንቀሳቀሱ አልሚዎችን ከተማ አስተዳደሩ ያበረታታል” -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

10

ሰኔ 3 ቀን 2014 (ኢዜአ) በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የከተማዋን የቤት ችግር ለመፍታት የሚንቀሳቀሱ አልሚዎችን የከተማ አስተዳደሩ እንደሚያበረታታ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ18 ወራት ግንባታው የተጠናቀቀውን እና የፊታችን እሁድ የሚመረቀውን የገርጂ መኖሪያ መንደር ጎብኝተዋል።

ከንቲባ አዳነች በጉብኝታቸው ወቅት በአጭር ጊዜ እንደዚህ ዓይነት ግዙፍ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ መሰራቱ ለከተማዋ ውበት እና እድገት ትልቅ ነገር ነው ማለታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።