በማሠልጠኛ ማዕከላት የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 10 ሺህ ሜትር አትሌት አቤል በቀለ አሸነፈ

469

ሰኔ 2/2014/ኢዜአ/ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ባለው የማሠልጠኛ ማዕከላት የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በወንዶች 10 ሺህ ሜትር አትሌት አቤል በቀለ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነ።

ሁለተኛው የአትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከላት የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በዛሬው እለት ተጀምሯል።

በመጀመሪያ ቀን ተጠባቂው የ10 ሺህ ሜትር የወንዶች የፍጻሜ ሩጫ ውድድር ተካሂዶ አቤል በቀለ ከተንታ ማሠልጠኛ ቀዳሚ ሆኖ በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኗል።

ከተንታ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል አትሌት ታሪኩ አንተነህ እንዲሁም አትሌት ሃብታሙ ብርሃኑ ከደባርቅ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል እንደየ ቅደም ተከተላቸው ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

ከወንዶች 10 ሺህ ሜትር በተጨማሪ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር እና በዲስከስ ውርወራ የፍጻሜ ውድድር ተካሄዷል።

በወንዶች  ስሉስ ዝላይ ፋጻሜን ጨምሮ በተለያዩ ርቀቶች  የማጣሪያና የፍጻሜ ውድድሮች ይደረጋሉ።

ለሦስት ተከታታይ ቀናት በሚደረገው ውድድር ከሰባት ማዕከላት የተውጣጡ 155 ወንድና 131 ሴት አትሌቶች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም