ኢትዮ ቴሌኮም የፓስፖርት ክፍያን በቴሌብር መፈጸም የሚያስችል ስምምነት ከኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ተፈራረመ

101

ሰኔ 2 ቀን 2014 (ኢዜአ)ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የፓስፖርት ክፍያን በቴሌብር መፈጸም የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን ዛሬ የኢትዮ- ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እና የኢሚግሬሽን ና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩህተስፋ ሙሉጌታ ተፈራርመዋል።

በዚህም ስምምነቱ በቴሌ ብር አማካኝነት አዲስ ወይም የጠፋ ፓስፖርትን ለማውጣት ክፍያ መፈጸም ያስችላል ነው የተባለው፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ኢትዮ ቴሌኮም ቴሌ-ብር መተግበሪያን ተግባራዊ ካደረገ ጀምሮ 20 ሚሊዮን የሚደርሱ ደንበኞችን ማፍራት ችሏል፡፡

በቴሌ ብር አማካኝነት 20 ቢሊዮን ብር የሚደርስ የገንዘብ ዝውውር መደረጉንም ነው የተናገሩት፡፡

ኩባንያው ለደንበኞቹ ቀልጣፋ፣ ፈጣን እና ጊዜ ቆጣቢ የሆኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑም በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም