ብሄራዊ የምግብና ስርዓተ ምግብ ስትራቴጂ መድረክ በሀዋሳ እየተካሄደ ነው

82

ሀዋሳ ሰኔ 02/2014 (ኢዜአ)...ብሄራዊ የምግብና የስርዓተ ምግብ ስትራቴጂ እና የሲዳማ ክልል የምግብና የስርዓተ ምግብ ጉባዔ ይፋ ማድረጊያ መድረክ በሀዋሳ ከተማ አየተካሄደ ነዉ።

መድረኩ እየተካሄደ ያለዉ "ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን በ2022ዓ.ም ከመቀንጨር ችግር ነፃ ለማድረግ እንተጋለን" በሚል መሪ ሀሳብ ነው።

መሪ ሐሳቡ ኢትዮጵያ ለማሳካት በርካታ ተግባራት ስታከናውንበት ከነበረው የሰቆጣ ቃል ኪዳን የተቀዳ መሆኑም ተመላክቷል።

ከብሔራዊ የምግብና ስርዓተ ምግብ ስትራቴጂ ምክክር በተጓዳኝ የሲዳማ ክልል የምግብና የስርዓተ ምግብ ጉባዔም ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።

በህጻናት ህይወት ላይ የመጀመሪያዎቹ 1 ሺህ ቀናት የመቀንጨር ችግር ለመፍታት ወሳኝ ጊዜያት መሆኑም ተመላክቷል።

ለሁለት ቀናት በተዘጋጀው በዚሁ መድረክ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማን ጨምሮ ከሚኒስቴሩና ከሲዳማ ክልል የከተማ አሰተዳደርና ወረዳዎች የተውጣጡ አመራሮች አንዲሁም በጤና ዙሪያ የሚሰሩ አካላት እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም