አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሾሙ

4

ሰኔ 02 ቀን 2014 (ኢዜአ) አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

አምባሳደር ተስፋዬ ሰኔ 01 ቀን 2014 ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እስከተሾሙበት ድረስ በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡