በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በኢንቨስትመንትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ

180

ግንቦት 30 ቀን 2014 (ኢዜአ)በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ የሚመራ ልኡክ ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በኢንቨስትመንትና ሌሎች ተያያ ዥ ጉዳዮች ዙሪያ በባህር ዳር ከተማ መከሩ።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ በውይይቱ ወቅት እንዳሉት የቱርክ ባለሃብቶች በክልሉ በኢንቨስትመንትእና በፕሮጀክት አስተዳደር ላይ እየተሳተፉ ነው።

May be an image of 3 people, people sitting, suit and indoor

ለአብነትም የአባይ ድልድይ ግንባታ ላይ በማማከር፣በምስራቅ አማራ እየተገነባ ባለው የባቡር መንገድ በተቋራጭነትና ሌሎች የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እየተሳተፉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የአማራ ክልል በእርሻ፣በማእድን፣በጨርቃጨርቅ፣በቱሪዝምና ሌሎች የኢንዱስትሪ ዘርፎች እምቅ ሃብት ያለው መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ለልኡካን ቡድኑ አስረድተዋል።

ቱርክ በፊልም፤በሙዚቃ እና ሌሎች የባህል ልማቶች ሰፊ ልምድ ያላት አገር በመሆኗ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማሳደግ ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል ተናግረዋል።

የቱርክ ባለሃብቶች ያላቸውን እውቀት፣ልምድና ክህሎት ተጠቅመው ወደ ክልሉ ኢንቨስት ለማድረግ ቢመጡ የክልሉ መንግስት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን አስረድተዋል።

በኢትዮጰያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ በበኩላቸው በርካታ ባለሃብቶች በአማራ ክልል በኢንቨስትመንት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በጨርቃ ጨርቅ፣በጥጥ ልማት፣በመሰረተ ልማት ግንባታና በሌሎች ዘርፎች በስፋት እየተሳተፉ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

በቀጣይም አሁን ያለውን መልካም ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር የጋራ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እንሰራለን ሲሉ አምባሳደሯ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም