ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

100

ግንቦት 30 ቀን 2014 (ኢዜአ)ባሳለፍነው ሳምንት 110 ሚሊዮን 66 ሺህ ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ባደረገው ክትትል 87 ነጥብ 9 ሚሊዮን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 22 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች፤ የጦር መሳሪያዎች፣ጫት፣አደንዛዥ እጾች፣የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

May be an image of money

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በብርበራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን ኮንትሮባንድ ሲያዘዋዉሩ የተገኙ ሰባት ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች፣የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህብረተሰብ ምስጋና ማቅረቡን ከጉምሩክ ኮሚሽንያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም