ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ አዲስ የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች ግንባታን አስጀመሩ

106

ግንቦት 30 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ አዲስ የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች ግንባታን በይፋ አስጀመሩ፡፡

አጠቃላይ 36 ቤቶች ግንባታ ያስጀመሩ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 28 የንግድ ቤቶች እና 8 መኖሪያ ቤቶች ይገኙበታል።

ግንባታው በአንድ ወር እንደሚጠናቀቅ የተገለፀ ሲሆን ወጪውም በሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እንደሚሸፈን ተጠቅሷል፡፡

May be an image of 4 people and outdoors

ከንቲባ አዳነች አቤቤ “የምንሰራቸውን የልማት ስራዎች አጠናክረን እንቀጥላለን” ሲሉ ገልጸው ለሚሰሩ የልማት ስራዎች የባለሀብቶች ተሳትፎ የላቀ ነው ብለዋል።

"ሁላችንም ዜጎች ተባብረን ለአንድ አላማ ከሰራን ሀገሪቱ የማትለወጥበት ምንም አይነት ምክንያት አይኖርም" ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ግንባታው ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግበት የተገለጸ ሲሆን ቤቶቹ ሲጠናቀቁ አቅም ለሌላቸው ወገኖች እንደሚተላለፉ ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም