ኢዜአ ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ካበረከተው የመጽሃፍት ድጋፍ ባሻገር ለመጽሃፍ ማሰባሰብ ዘመቻው ሰፊ ሽፋን በመስጠት የበኩሉን ኃላፊነት እየተወጣ ነው

188

ግንቦት 29/2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ካደረገው መጽሃፍት ድጋፍ ባሻገር ለመጽሃፍ ማሰባሰብ ዘመቻው ሰፊ ሽፋን በመስጠት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እየተወጣ መሆኑን የጠቅላይ ሚንስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሙአዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት ተናገሩ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በሁለተኛ ዙር ያሰባሰባቸውን 2 ሺህ መፅሐፍት ለአብሮሆት ቤተ-መፅሐፍት አስረክቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ሰይፈ ደርቤ፤ መፅሃፍቱን የጠቅላይ ሚንስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሙአዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረትን ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት አስረክበዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው በዚሁ ጊዜ፤የተበረከቱት መፅሐፍት የማህበራዊ ሳይንስ፤የተፈጥሮ ሳይንስ፤የቢዝነስ፣ የስነጥበብ፣ የኪነጥብ ስነፅሁፍና የታሪክ ይዘት ያላቸው እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

መፅሐፍቶቹ በአዲስ አበባ ከዋናው መስሪያ ቤትና ከክልል ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ሰራተኞች የተሰበሰቡ መሆናቸውንም እንዲሁ፡፡

በሁለተኛ ዙር ከተበረከቱት መጽሀፍት መካከል የታዋቂው የኪነ-ጥበብ ሰው የአርቲስት ደበበ እሸቱ ባለቤት ወይዘሮ አልማዝ ደጀኔ 210 መጽሀፍትን መለገሳቸውንም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም  ሀዋሳ በሚገኘው የተቋሙ ቅርንጫፍ የሚሰራ ጋዜጠኛ ከመጽሃፍ በተጨማሪ የሶስት ሺህ  ብር ድጋፍ ማድረጉንም ገልጸዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስተሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል  ክብረት በበኩላቸው፤ አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ካበረከተው መጽሃፍት ባሻገር ለመጽሃፍ ማሰባሰብ ዘመቻው ሰፊ ሽፋን በመስጠት የበኩሉን ኃላፊነት እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለቤተ መጽሃፍቱ የሚደረገውን ድጋፍ የዜና ሽፋን በመስጠት ለዘመቻው መሳካት እየሰራ እንደሚገኝም ነው ያነሱት፡፡

ዓለም የውድድር ዘመን  ላይ ይገኛል፤ ውድድሩን ማሸነፍ የሚቻለው በእውነት እና በእውቀት ብቻ ነው ሲልም ነው የተናገረው፡፡

በመሆኑም መጽሀፍትን በመለገስ ትውልድን በእውነትና እውቀት ማነጽ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም