ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በመዲናዋ የሥጋ ደዌ ተጠቂ የሆኑ የማህበረሰብ አባላትን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቤት እድሳት አስጀመሩ

5

ግንቦት 29 ቀን 2014 (ኢዜአ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ለሚኖሩ የስጋ ደዌ ተጠቂ ማህበረሰብ አባላት ተጠቃሚ የሚያደርግ የቤት እድሳት አስጀመሩ፡፡

ከክረምት በፊት ተጠናቀው የሚያልቁ የስድስት አባወራ ቤቶችን እንደሚያድስ የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የቤት እድሳቱ በማህበረሰቡ ዘንድ የተዘነጉትን የስጋ ደዌ ተጠቂ ማህበረሰብ አባላት ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የቤት እድሳቱ ተጨማሪ ተጠቃሚዎችን በማካተት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።