ለጃራ አባገዳ ቅደመ መጀመሪያእና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ 54.4 ሚሊየን ብር ተመደበለት

49

አዲስ አበባ ግንቦት 29/2014 /ኢዜአ/ የጃራ አባገዳ ቅደመ መጀመሪያ እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ 54.4 ሚሊየን ብር ማስፋፊያ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ ።

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ማስፋፊይ የሚደረግለት የጃራ አባገዳ ቅደመ መጀመሪያ እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 54.4 ሚሊየን ብር በጀት ተይዞለታል።

የመሠረት ድንጋዩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አስቀምጠዋል።

ትምህርት ቤቱም በስምንት ወር ተገንብቶ ለአገልግሎት ይበቃል ብለዋል ።

የመማሪያ ክፍሎች፣ቤተ መከራ ፣ ቤተመጽሃፍትና የተለያዩ የአስተዳደር ክፍሎች የሚሟሉለት መሆኑ ተገልጻል ።

ትምህርት ቤቱ ከተመሠረተ 3 አመት ማስቆጠሩና የማስፋፋያ ግንባታው ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት እንደሚያግዝም ተገልጿል።