ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ትግራይ ክልል የሚሄደውን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቀላጠፍ የሚደረገውን ጥረት በሰርዶ ኬላ ተገኝተው ተመለከቱ

330

ሠመራ፣ ግንቦት 27 ቀን 2014 (ኢዜአ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ትግራይ ክልል የሚሄደውን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቀላጠፍ የሚደረገውን ጥረት በአፋር ክልል ሰርዶ ኬላ ተገኝተው ተመለከቱ።

በጉብኝቱ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አወል አርባ እንዲሁም ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መንግስት ወደትግራይ ክልል የሚላኩ ሰብአዊ እርዳታዎች ለማሳለጥ እያደረገ ከሚገኘዉ ሁሉን አቀፍ ጥረት በተጓዳኝ አሸባሪው ህወሃት ለጥፋት አላማው ሊጠቀምባቸዉ የሚችሉ ቁሳቁሶች እንዳይተላለፉ በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።

ባለድርሻዎችም  ትኩረት እንዲሰጡም አስገንዝበዋል።

በሽብር ቡድኑ ወረራ ምክንያት የአፋር ህዝብ ከ1 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ተፈናቃዮችን ይዞ መንግስት ለትግራይ ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ እያደረገ የሚገኘዉን ጥረት ተፈጻሚነት ያሳየዉ ቀናት ትብብር እሚደነቅ ነዉ

ለዚህም በየደረጃዉ የሚገኙ አመራሮች የሃገር ሽማግሌዎች፣ ሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ማህበረሰብ መሪዎች እንዲሁም  የክልሉ ነዋሪ ሊመሰገን ይገባል

መንግስት በተለያዩ ክልሎች በሰዉ ሰራሽና የተፈጥሮ  አደጋዎች ምክንያት የተጎዱ ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ ከተያዩ ባለድርሻዎች ጋር በመሆን ለመደገፍ በትኩረት አየሰራ ነዉ

ከዚህም ውስጥ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች አንዱ መሆኑን ገልጸዉ ለተገጂዎች ያልተገደበ ሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትን የበለጠ ለማሳለጥ ለአለም ምግብ ድርጂትና ሌሎች አጋሮች ጋር በቅንጂት አየተሰራ ነዉ

የሰብአዊ እርዳታዉ በቀን እስከ 200ኮንቦይ ተሽከካሪ በሰርዶ ኬላ ተገቢዉ የፍተሻና ተያያዥ ቁጥጥር ከተደረገበት በኋላ አንደሚላክ በጉብኝታቸዉ መረዳታቸዉን ገልጸዋል

ይሁንና በተደረገዉ ፍተሻም ለሽብር ቡድኑ የጥፋት አላማ ማስፈጸሚያ ሊዉሉ የሚችሉ ከተፈቀደዉ የነዳጅ መጠን በላይ ተጨማሪ ነዳጅና አንዳንድ ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶች ለማሳለፍ ሙከራዎች አንዳሉ መገንዘባቸዉን ገልጸዋል

ይህአይነት ተግባራት ከሰብአዊ አቅርቦት  ህጉ የሚጣረስ በመሆኑ ከሚመለከታቸዉ አካሎች ሰብአዊ አቅራቢ ድርጂቶዎች ጋር መንግስት አንደሚነጋገርበት አስረድተዋል

በአጠቃላይ መንግስት ሰብአዊ እርዳታዉን ለማሳለጥ ከሚያደረዉ ሁሉን አቀፍ ጥረቶች ጉን ለጎን ጉምሩክ ኮሚሺንና ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካሎች ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶች ላይ ተገቢዉን የቁጥጥርና ክትትል ስራቸዉን ሊጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል

መንግስት ለትግራይ ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ እያደረገ የሚገኘዉን ጥረት በመደገፍ እያሳየ ያለው ቀናንትና ትብብር የሚደነቅ ነው ብለዋል ሚኒስትር ደመቀ።

መንግስት በተለያዩ ክልሎች በሰዉ ሰራሽና የተፈጥሮ  አደጋዎች ምክንያት የተጎዱ ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ ከተለያዩ ባለድርሻዎች ጋር በመሆን ለመደገፍ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ለትግራይ ክልል ነዋሪዎች ‘ያልተገደበ ሰብአዊ እርዳታ’ አቅርቦትን የበለጠ ለማሳለጥ ከዓለም ምግብ ፕሮግራምና ከሌሎች አጋሮች ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

“በጉብኝታቸው የሰብአዊ እርዳታዉ በቀን እስከ 200 ኮንቮይ ተሽከርካሪ በሰርዶ ኬላ ተገቢዉ የፍተሻና ተያያዥ ቁጥጥር ከተደረገበት በኋላ እንደሚላክ ለመረዳት ችያለሁ” ብለዋል ሚኒስትሩ።

ይሁንና በሚደረገው ፍተሻም ለሽብር ቡድኑ የጥፋት አላማ ማስፈጸሚያ ሊዉሉ የሚችሉ ከተፈቀደዉ የነዳጅ መጠን በላይ ተጨማሪ ነዳጅና አንዳንድ ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶች ለማሳለፍ ሙከራዎች እንዳሉ  አመልክተዋል።

ይህ አይነት ተግባር ከዓለም አቀፍ ሰብአዊ ሕጎች ጋር የሚጣረስ በመሆኑ መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ ከሰብአዊ እርዳታ  አቅራቢ ድርጅቶችና ከሚመለከታቸው አካላት  እንደሚወያይ ገልጸዋል።

መንግስት ሰብአዊ እርዳታዉን ለማሳለጥ ከሚያደርገዉ ጥረት ጎን ለጎን ጉምሩክ ኮሚሽንና ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካሎች ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶች ላይ ተገቢዉን የቁጥጥርና ክትትል ስራቸዉን  ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም