ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ከ10 ሺህ በላይ መጻሕፍት አበረከተ

2

ግንቦት 27 ቀን 2014 (ኢዜአ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለሁለተኛ ጊዜ ያሰባሰባቸውን 10 ሺህ 100 መጻሕፍት ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት አበረከተ።

መጻሕፍቱን ያስረከቡት የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው ናቸው።

ኮርፖሬቱ ከዚህ ቀደም 2 ሺ 400 መጻሕፍት ያበረከተ ሲሆን በጠቅላላው 12 ሺህ 500 መጻሕፍት በሁለት ዙር ለአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት አስረክቧል።

መጻሕፍቱ ታሪክ፣ ሳይንስና ጥበብን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ ሲሆኑ በአገር ውስጥና በውጭ ቋንቋዎች የተጻፉ ናቸው።

ኮሪፖሬቱ መጻሕፍቱን ያሰባሰበው ከተቋሙ ሰራተኞች፣ ከአድማጭ ተመልካች እንዲሁም ከአጋሮቹ መሆኑ ታውቋል።

ዛሬ ከተበረከቱት መጻሕፍት ውስጥ ወደ 4 ሺህ የሚሆኑት በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የክልል ኤፍ. ኤሞች በኩል የተሰበሰቡ ነው።