ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ሠመራ ገቡ

5

ግንቦት 27 ቀን 2014 (ኢዜአ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አፋር ሠመራ ገቡ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሠመራ ሱልጣን አሊሚራህ ሃንፈሬ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በአፋር ክልል በሚኖራቸው ቆይታ ከክልሉ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት  እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።