ሀገር አቀፍ የምህንድስናና ቴክኖሎጂ አውደ ጥናት በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው

477

አርባምንጭ፤ ግንቦት 26/2014 (ኢዜአ) 3ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የምህንድስናና ቴክኖሎጂ አውደ ጥናት በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው፡፡

አውደ ጥናቱ "የምህንድስናና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ለዘላቂ ልማትና ተግዳሮቶች" በሚል መሪ ሀሳብ  እየተካሄደ ነው ፡፡

ዘርፉን ለማዘመን እንደ ሀገር እየተደረገ ያለውን ጥረት ከስኬት ለማድረስ የሚያግዙ የምርምር ውጤቶች ማፍለቅ  የአውደ ጥናቱ ዓላማ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

 በአውደ ጥናቱ 22 የጥናትና ምርምር ሥራዎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል፡፡

በመድረኩም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳምጠው ዳርዛን ጨምሮ ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመጡ ምሁራንን በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር፣ ስኳር ፋብሪካዎች፣ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን፡ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣንና ሌሎች አካላት እየታደሙ መሆኑ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም