ጋዜጠኛ ሕይወት ታደሰ ያሰባሰበችውን 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል ድጋፍ አደረገች

94


ግንቦት 26 ቀን 2014 (ኢዜአ) በሰሜን አሜሪካ ነዋሪ የሆነች ጋዜጠኛ ሕይወት ታደሰ በማኅበራዊ ሚዲያ ያሰባሰበችው 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል ድጋፍ አደረገች።

ጋዜጠኛዋ "ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ ይቀላቀላሉ" በሚል መሪ ኃሳብ ነው ገንዘቡን ያሰባሰበችው ተብሏል።

ጋዜጠኛዋ ከማኅበራዊ ሚዲያ ያሰባሰበችውን 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በዛሬው ዕለት በተወካይ በኩል ለማዕከሉ አስረክባለች።


የማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሕሩይ አሊ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

ሚዲያዎች ዜጎች የልብ ሕሙማን ለማገዝ የሚችሉባቸውን መንገዶች በማስተዋወቅ ረገድ የጀመሩትን ሥራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።


በርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ የጋዜጠኛዋ ቤተሰቦች፣የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል አመራሮች፤የሕክምና ባለሙያና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።


የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ለታካሚዎች ነፃ የልብ ሕክምና አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ተቋም ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም