የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለ55 ፖሊስ መኮንኖች የስትራቴጂክ የማዕረግ እድገት ሰጠ

284


ግንቦት 26 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለ55 ፖሊስ መኮንኖች የስትራቴጂክ የማዕረግ እድገት ሰጠ።


በመርሀ ግብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተገኝተዋል።


የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እንዳሉት የማዕረግ ዕድገት የተሰጣቸው መኮንኖች በተግባር ተፈትነው የተሻለ የአመራር ብቃት ያሳዩ ናቸው።


በያዙት ማዕረግ ከአራት ዓመት በላይ ያገለገሉ፣ የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ያላቸው እንዲሁም አርዓያ የሚሆን ፖሊሳዊ ስብዕና ያላቸው በሚል የተለዩ መሆናቸውን ገልጸዋል።


የማዕረግ ዕድገት ከተሰጣቸው መኮንኖች መካከል 12ቱ ከረዳት ኮሚሽነርነት ወደ ምክትል ኮሚሽነርነት ያደጉ ሲሆን 43ቱ ከኮማንደር ረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ ያገኙ ናቸው።


ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም