‘ፎርተስኪው ፊዩቸር ኢንዱስትሪስ’ በኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችለውን የኢንቨስትመንት ፈቃድ አገኘ

5

ግንቦት 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) ‘ፎርተስኪው ፊዩቸር ኢንዱስትሪስ’ የተሰኘው የአውስትራሊያ የማዕድን ኩባንያ በኢትዮጵያ በማዕድን ለመሰማራት የሚያስችለውን የኢንቨስትመንት ፈቃድ አገኘ።

የኩባንያው ፈቃድ መሰጠቱን ይፋ የማድረግ መርሃ-ግብር ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ ተካሄዷል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ያለውን የታዳሽ ኃይል ሃብት በመጠቀም የካርበን ልቀት የሌለው አረንጓዴ ሃይድሮጅንና አሞኒያ ልማት ላይ እንደሚሰማራ ተጠቅሷል።

በፈቃዱ አማካኝነት ኩባንያው የሚያመርተው አረንጓዴ ሃይድሮጅንና አሞኒያ (ነዳጅ) ለተለያዩ ከፍተኛ ነዳጅ ኃይል ለሚጠቀሙ ኩባንያዎች፣ ተሽከርካሪዎች፣ ባቡሮችና ለአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ግብአትነት ይውላል ተብሏል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ሥራ መጀመሩ ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ላይ የተመሰረተ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፈው የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ገልጸዋል።

ፎርተስኪው ፊዩቸር ኢንዱስትሪስ ኩባንያ እ.አ.አ በ2003 የተቋቋመ ሲሆን፤ ኩባንያው በታዳሽ ኃይል ልማት ላይ የሚሰራ ነው።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ