በኢትዮጵያ በበጎ ፈቃድ ተግባራት 7 ቢሊየን ብር የልማት ስራ ተከናውኗል

106

ግንቦት 25 ቀን 2014 (ኢዜአ)በኢትዮጵያ 21 ሚሊየን በላይ ዜጎች ባከናወኗቸው የበጎ ፈቃድ ተግባራት 7 ቢሊየን ብር የሚገመት የልማት ስራ መከናወኑን ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ አስታወቁ።

ሚኒስትራ ይህን የገለጹት ዓለም አቀፉ የ2022 በጎ ፈቃደኞች ሪፖርት ይፋ በሆነበት ወቅት ነው።

ሪፖርቱም በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መሰብሰቢያ አዳራሽ "እኩልነትና አካታችነት ለማህበረሰብ ግንባታ" በሚል መሪ ሀሳብ እየቀረበ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣በኢትዮጵያ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስራ ኃላፊዎች፣በጎ ፈቃደኛ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጨምሮ ሌሎች አካላት ተገኝተዋል።

በዚሁ ወቅት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ በኢትዮጵያ 21 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ባከናወኗቸው የበጎ ፈቃድ ተግባራት 7 ቢሊዮን ብር የሚሆን የልማት ስራ ተከናውኗል ብለዋል።

በደን ልማትና አካባቢ ጥበቃን ጨምሮ፣በፈጠራ፣በትምህርት፣በጤና፣ በግብርና ልማት፣ ኮቪድ ወረርሽኝ መከላከልና ሌሎች ዘርፎች ላይ የልማት ስራ የተከናወኑባቸው ዘርፎች እንደሆኑም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም