የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የባህል ፌስቲቫልና አውድ ርዕይ በቦንጋ ተከፈተ

92

ሚዛን አማን፣ ግንቦት 25/2014 (ኢዜአ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የባህል ፌስቲቫልና አውደ ርዕይ በቦንጋ ተከፈተ።

"ባህላችን ለዘላቂ ሰላማችን እና ለአንድነታችን" በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው  የባህል ፌስቲቫልና አውደ ርዕይ እስከ ግንቦት 27/2014 ዓ.ም ድረስ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ተመላክቷል።

ከሁሉም ዞኖች የተወጣጡ የባህል ቡድኖች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች በፌስቲቫሉና አውድ ርዕዩ  እየተሳተፉ ነው።

የባህል ፌስቲቫልና አውደ ርዕዩ የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ነፊሳ አልማሂዲን  ጨምሮ የተለያዩ የፌደራልና የክልል የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የባህላዊ አልባሳት፣ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎችና፣ምግብና መጠጦች እየተጎበኙ ነው።

በባህል ፌስቲቫልና አውደ ርዕዩ  በክልሉ የሚገኙ 13 ብሔረሰቦች ባህላቸውን በማስተዋወቅ እየተሳተፉ መሆኑን ሪፖርተራችን ከሥፍራው ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም