በኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ በአራተኛ ቀን ውሎው የተለያዩ የፍፃሜ ውድድሮች ተከናውነዋል

434

አዲስ አበባ ግንቦት 25/2014 /ኢዜአ/ በኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ በአራተኛ ቀን ውሎው የተለያዩ የፍፃሜ ውድድሮች ተከናውነዋል።

በወንዶች የሱሉስ ዝላይ የፍፃሜ ውድድር አትሌት ዮሴፍ ኦባንግ 15  ነጥብ 44  ሜትር በመዝለል የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት ሆኗል።

እድሜቸው  ከ18  ዓመት በታች የሆኑ አትሌቶች እየተሳተፉበት ባለው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ በ15 የስፖርት አይነቶች ውድድር እየተካሄደበት ይገኛል።

በዚህ ውድድር የተለያዩ የፍፃሜ ጨዋታዎች እየተካሄዱ ሲሆን በወንዶች የሱሉስ ዝላይ ከደቡብ ክልል አትሌት ዮሴፍ ኦባንግ 15  ነጥብ 44  ሜትር በመዝለል የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት ሆኗል።

የጋምቤላ ክልል ተወዳዳሪው አትሌት ኡመድ ኡጅሉ 15  ነጥብ 09 ሜትር በመዝለል ሁለተኛ ሲሆን አትሌት ኡሙድ ኦባሳ ከአዲስ አበባ 15  ነጥብ 08 ሜትር በመዝለል ሶስተኛ ጀረጃን ይዞ አጠናቋል።

በውድድሩ ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን በሌሎች የስፖርት አይነቶችም አሸናፊዎች የሚለዩበት ይሆናል።

ከግንቦት 21 ጀምሮ እስከ ሰኔ 4 ቀን በሚካሄደው የኦሊምፒክ ውድድር ከተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ4 ሺህ በላይ ተወዳዳሪዎች እየተሳተፉበት ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም