ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የልማት እንቅስቃሴዎች ለመጎብኘት ባሌ ሮቤ ገቡ

202

ግንቦት 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የባሌ ዞን የልማት እንቅስቃሴዎች ለመጎብኘት ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሮቤ አየር ማረፊያ ሲደርሱ አባ ገዳዎች፣ሃደ ሲንቄዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በቆይታቸውም የአካባቢውን የአርብቶ አደር ማህበረሰብ የድርቅ ተጋላጭነት ይቀንሳል ተብሎ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የዌልመል ዘመናዊ መስኖ ፕሮጀክት ግንባታን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዞኑ እየተካሄዱ ያሉ የበልግ እርሻና የበጋ መስኖ ልማቶችም የጉብኝቱ አካል ናቸው ተብሏል።

የዌልመል ዘመናዊ የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠና እየተገነባ መሆኑ ይታወሳል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም