የኦሮሚያ ክልል ከ10 የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ጋር ስምምነት ተፈራረመ

204

ግንቦት 24 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኦሮሚያ ክልል የሲሚንቶ ዋጋ መናር መግታትና መከላከል ያስችለኛል ያለውን ስምምነት ከ10 የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ጋር ተፈራረመ።

ስምምነቱ ፋብሪካዎቹን ሲሚንቶ ምርት ከሚሸጡላቸው ኤጀንሲዎች ጋር ያላቸውን ውል በማቋረጥ በጥቃቅንና አነስተኛ ከተደራጁ ማህበራት ጋር እንዲተሳሰሩ የሚያደርግ እንደሆነ ተገልጿል።

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲና የፋብሪካዎቹ ተወካዮች ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ ፋብሪካዎቹ ሲሚንቶ በሙሉ አቅም እንዲያመርቱና ምርታቸውን ከሚሸጡላቸው ኤጀንሲዎች ጋር ያላቸውን ውል አቋርጠው ምርታቸውን በአነስተኛና ጥቃቅን ለተደራጁ ማህበራት እንዲያቀርቡ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

May be an image of 3 people and indoor

ምርት የሚቀርብላቸው 300 ማህበራት ስራ አጥ ወጣቶች፣ የተቸገሩ ወገኖችና በተለያዩ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች መሆናቸው ተነግሯል።

ውላቸው እንዲቋረጥ የተባሉት ኤጀንሲዎች ደላሎችን በሲሚንቶ ሽያጭ ውስጥ እንዲሳተፉ በማድረግ የዋጋ ንረት እንዲከሰት ማድረጋቸው ተጠቅሷል።

በስምምነቱ መሰረት ፋብሪካዎቹ ሲሚንቶ የሚሸጡት የኦሮሚያ ክልል ባወጣው የዋጋ ተመን የትራንስፖርት ዋጋ ብቻ በመጨመር እንደሆነ ነው የተገለጸው።

የኦሮሚያ ክልል የሲሚንቶን ዋጋ ንረትን አስመልክቶ ባደረገው ጥናት መሰረታዊ የሚባሉ ችግሮች መለየታቸው በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

ፋብሪካዎች ከሕገ-ወጥ ደላሎች ጋር በመመሰጣር ከአቅማቸው በታች ምርት በማምረት የምርት እጥረት እንዲከሰት ማድረግ፣ የጸጥታ ችግር፣ አላስፈላጊ የኬላዎች መብዛትና በስርጭት ውስጥ የሚሳተፉ ሕገ-ወጥ ደላሎች ለዋጋ መናሩ መንስኤ ናቸው ተብሏል።

የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚሰራና የስርጭት ችግሩን ለመፍታት ኤጀንሲዎች ከሽያጭና ማከፋፈል ውጪ እንደሚሆኑ አመልክቷል።

May be an image of 1 person

በስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኦሮሚያ ክልል ተግባርን በአገር አቀፍ ደረጃ ማስፋት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም