የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ የአትሌቲክስ ውድድር ተጀምሯል

411

ግንቦት 23/2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ የአትሌቲክስ ውድድር ተጀምሯል።

በሐዋሳ እየተካሄደ በሚገኘው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ የአትሌቲክስ ውድድር ተጀምሯል።

ከተጀመረ ሶስተኛ ቀኑን በያዘው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ በተለያዩ ስፖርቶች የፍፃሜና የማጣሪያ ውድድሮችም ተካሂደዋል።

በዛሬው እለት ከተካሄዱት ጨዋታዎች መካከል በሁለቱም ፆታ የ3 ሺህ ሜትር ሩጫ የፍፃሜ ውድድሮች ተካሂደዋል።

በወንዶች የ3 ሺህ ሜትር ውድድር አትሌት ሐሊፎም ተስፋዬ ከአዲስ አበባ ከተማ  የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሲሆን አትሌት ቀሬንሶ ደገፉ ከኦሮሚያ ክልል ሁለተኛ እንዲሁም ሙቤን ሐጂ ከአዲስ አበባ ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል።

በሴቶች የ3 ሺህ ሜትር ውድድር አትሌት መቅደስ አለምሸት ከደቡብ ክልል ቀዳሚ ስትሆን አትሌት የኔነሽ ሽመክትና አትሌት ዝይን አለልኝ ከአዲስ አበባ እንደ ቅደም ተከተላቸው ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው የሜዳሊያ አሸናፊዎች ሆነዋል።

ከሩጫ ውድድሮች በተጨማሪ በሁለቱም ፆታዎች የብስክሌት የፍጻሜ  ውድድሮችም ተደርገዋል።

የካራቴና የጠረጴዛ ቴንስ ስፖርትን ጨምሮ በተለያዩ ስፖርቶች የማጣሪያ ጨዋታዋችም ተከናውነዋል።

በኦሎምፒኩ ከተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ4 ሺህ በላይ ስፖርተኞች የተሳተፉ ሲሆን እስከ ሰኔ 4  ቀን 2014 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል።   

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም