የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር በሲዳማ ክልል አስተናጋጅነት ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር በሲዳማ ክልል አስተናጋጅነት ተጀመረ
220
ግንቦት 21 ቀን 2014 (ኢዜአ) የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር በሲዳማ ክልል አስተናጋጅነት በሀዋሳ ከተማ ዛሬ ተጀመረ።
ለ15 ቀናት በሚቆየው በዚህ የኦሎምፒክ ውድድር ከሁሉም ክልሎች፣ ከአዲስ አበባና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ከ4 ሺህ በላይ ስፖርተኞች በ15 የተለያዩ የውድድር ዘርፎች ተሳታፊ ይሆናሉ።
በስነስርዓቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የአለም፣ የኦሎምፒክ አትሌቲክስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፖልተር ጋት እንዲሁም የክልልና የፌዴራል አመራሮች ተገኝተዋል።