በሀገር አቀፉ የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ለመታደም እንግዶች ሐዋሳ እየገቡ ነው

52

ግንቦት 21 ቀን 2014 (ኢዜአ)በሀገር አቀፉ የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ላይ ለመታደም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉ-ባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገርና የአለም የኦሎምፒክ አትሌቲክስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፖልቴር ጋት ሀዋሳ ገብተዋል።

ሀገር አቀፍ የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ዛሬ ከሰዓት በሐዋሳ ይጀምራል።
ከግንቦት 21- ሰኔ 5/2014ዓ.ም ድረስ የሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ሐዋሳ እየገቡ ላሉ እንግዶች የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የአፍርካ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዋና ፀሀፊ፣ የብሩንዲ ኦሎምፒክ ፕሬዚዳንትና የአፍርካ ኦሎምፒክ ስራ አስፈጻሚ፣ የደቡብ ሱዳንና፣ የኤርትራ ኦሎምፒክ ፕሬዚዳንቶች፣የአፍሪካ ዞን 5 ዓቃቤ ንዋይና ሌሎች ሌሎች እንግዶች በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱን ለመታደም ሐዋሳ ገብተዋል።