በመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችና መፍትሄዎችን በሚመለከት በተደረገ ጥናት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

50

ግንቦት 21 ቀን 2014 (ኢዜአ) በመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች እንዲሁም የመፍትሔ አማራጮችን ለማመላከት በተደረገ ጥናት ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።

በውይይቱም በአዲስ አበባ ከተማ የመንግስትን ሀብት ለማልማት እንቅፋት የሚሆኑ በፍርድ ቤት ጊዜያዊ ዕግዶች በኩል የሚስተዋሉ ችግሮችን በጋራ መፍታት ይጠይቃል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚከራከርባቸውን የመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች እና የጊዜያዊ ዕግዶችን በተመለከተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተጠና ሰነድ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።

ጥናቱ በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች፣የመፍትሔ አማራጮችና የትግበራ መመሪያዎችን ማካተቱ ተጠቁሟል።

የፍትህ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች፣የፍርድ ቤቶች ዳኞች፣ የተወካዮች ሞክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ አቃቤያነ ሕጎችና ሌሎች የፌዴራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የከተማው ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ፅዋዬ ሙሉነህ በበኩላቸው የከተማዋን ሁለንተናዊ ልማት ለማከናወን መጓተት ከሚፈጥሩት ችግሮች መካከል አንዱ የፍርድ ቤቶች ጊዜያዊ ዕቅዶች ናቸው ብለዋል።

በመሆኑም የተቀላጠፈ፣ፍትሀዊ እና የመንግስት ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም እንቅፋት የሚሆኑ ችግሮችን ለይቶ ለውይይት ያቀረበ ጥናት እንደሆነ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መድረኩ ጥናትን መሰረት ያደረገ አካሄድ ለመያዝና ከተማችንን በጋራ ለማልማት ያለመ ነው ብለዋል።