የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ አሸናፊነት የሚያንፀባርቅ ነው የተባለ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ በሀረር ከተማ ተከፈተ

124

ሀረር፤ ግንቦት 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) "ስለ ኢትዮጵያ " በሚል መሪ ሀሳብ የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ አሸናፊነት የሚያንፀባርቅ ነው የተባለ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ በሀረር ከተማ ተከፈተ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከጅግጅጋ እና ድሬደዋ በመቀጠል ሐረር ከተማ ላይ ዛሬ ያዘጋጀውን የፎቶ አውደ ርዕይ፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እና የመገናኛ ብዙሀን ባለስንጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ እድሪስ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ከፍተውታል።

የፎቶ አወደ ርዕዩ ከ1960 ዎቹ ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያን ተስፋ እስከጣለችበት የሪፎርም ለውጥ ማግስት ያለውን ሁለንተናዊ ገፅታ በሚያሳይ መልኩ ለህዝብ እይታ ቀርቧል።

ለአራት ቀናት በሚዘልቀው በዚህ የፎቶግራፍ አውደርእይ ላይ የምስራቅ ተጎራባች ክልሎች አመራሮች፣ ባለሀብቶች፣ አባገዳዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች ተሳታፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም