ኢትዮ ቴሌኮም እና ሀይብሪድ ዲዛይን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ክፍያዎችን በቴሌ ብር ለመፈፀም የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮ ቴሌኮም እና ሀይብሪድ ዲዛይን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ክፍያዎችን በቴሌ ብር ለመፈፀም የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

ግንቦት 18/2014/ኢዜአ/ ኢትዮ ቴሌኮም እና ሀይብሪድ ዲዛይን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በራይድ ትራንስፖርት በኩል የቴሌኮም አገልግሎትና ሌሎች ክፍያዎችን በቴሌ ብር ለመፈፀም የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።
የኢትዮ- ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህወት ታምሩ እና የሀይብሪድ ዲዛይን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳምራዊት ፍቅሩ ስምምነቱን ተፈራርመዋል።
በስምምነቱ መሰረት አዲስ ወይም የጠፋን ሲም ለማውጣት፣ የተበላሸን ለመቀየር፣ ገንዘብ ለማውጣት፣ ለማስቀመጥ እንዲሁም ሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌ ብር መፈፀም የሚቻል ይሆናል።
በሁሉም የራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ተሽከርካሪዎች የቴሌ ብር አገልግሎት ተግባራዊ ይሆናል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህወት ታምሩ፤ በኢትዮጵያ የዲጂታል ገበያን ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት እንዲህ አይነት ስምምነቶች ወሳኝነት አላቸው ብለዋል።