የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንገድ ትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅን በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ

125

ግንቦት 18 ቀን 2014 (ኢዜአ)የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንገድ ትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅን በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ።

ምክር ቤቱ ስድስተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ አካሄዷል።

የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ የመንገድ ትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ አቅርበዋል።

ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ በሶስት ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

የጸደቀው አዋጅ ቁጥር 1274/2014 ስያሜ ተሰጥቶታል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ያቀረቡትን የተቋማቸውን የ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት የ10 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም